Advertisements
Advertisements

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Esubalew Yetayew - Chaw Tilina | New Ethiopian Music 2022 (Official Video)

Added by FanoTubers
Advertisements

Ethiopian Music : Esubalew Yetayew (Yeshi) | እሱባለው ይታየው /የሺ/ - Chaw Tilina | ቻው ትልና - New Ethiopian Music 2022 (Official Video)
________________________________________________________________________________________________
ግጥም
ቻው ትልና
ቀን ሲያልፍ አመረረች በቃ አትመጣም
አንሶባታል የፍቅሬ ጣዕም
ከእንግዲ እኔም ልተው ከተወቺኝ
ፍቅሬን ትታ ከረሳችኝ
በአደባባይ ቆሜ ስለምናት
ማሰብ ከብዶኝ እሷን ማጣት
ጭላንጭል ተስፋ እንኳ በሷ ጉዳይ
የሚያሳየኝ በር ባላይ
ቻው “ቻው ቻው” ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ
ደሞ ትመጣለች ያለ’ኔ አልችል ብላ
ቻው “ቻው ቻው” ትልና በቃህኝ በቃህኝ
ደሞ ትመጣለች አይንህ ላፈር ብላኝ
እረ ጉድ ናት !
ዞሬ ከእግሯ ስር ስር ከደጇፏ
አይደለችም ልክ እንዳፏ
ስትመጣ ተቀባይ ሸኚ ስትሄድ
ሆኗል ልቤ አሽከር መንገድ
ምን እንደሚያለያየን አላውቅም
ስትመጣም አልጠይቃትም
መውደድ አስሮ ገዝቶ ለጉሞኛል
እንደ ግዑዝ አስቀምጦኛል
ቻው “ቻው ቻው” ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ
ደሞ ትመጣለች ያለ’ኔ አልችል ብላ
ቻው “ቻው ቻው” ትልና በቃህኝ በቃህኝ
ደሞ ትመጣለች አይንህ ላፈር ብላኝ
እረ ጉድ ናት !
ልቤን በ’ጁ ፍቅር እየዘወረው
ትንፋሽ ውስጤን እያጠረው
እኔ እያልኩ ለሰዎች አሸማግሉኝ
እሷ እያለች ውይ ገላግሉኝ
ከዚኃላ ብዬ ተገዝቼ
ስትርቅ ካ’ይኔስንት ዝቼ
ገብቷት ማጠፊያ መዘርጊያው ልቤ
አልውል በሷ እንዳሳቤ
አሄሄ አሃሃ
አሄሄ አሃአሃአሃ
ጎራ እያለች ስዘጋጅ
እንዳለምድ ሌላ ወዳጅ
ሃሳቤን ስትሄድ አስታኝ
ወይ ትታ እረስታኝ
ዳኙኝ አዋዩኝ ‘ባካችሁ
የምታውቁ አፍቅራችሁ
እሷ ብልጥ የቆቅ ዘመድ
እኔ ያለኝ አንድ መውደድ
ቻል ቻል ቻል አድርጌው እንጂ
ባጣ ሰው አስረጂ
ቻው ቻው ብሎ የሄደ ሰው
መመለሱ ምነው ?
ቻው “ቻው ቻው” ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ
ደሞ ትመጣለች ያለ’ኔ አልችል ብላ
ቻው “ቻው ቻው” ትልና በቃህኝ በቃህኝ
ደሞ ትመጣለች አይንህ ላፈር ብላኝ
እረ ጉድ ናት !

Category
Music AMHARIC MUSIC

Post your comment

Comments

  • Salih
    Added

    Hajera

  • Bariso
    Added

    Waw

  • star
    Added

    I love this music